Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (2023)

Table of Contents
የጤፍ ዋጋ ንረቱ ነዋሪውን አስመርሮታል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተጣለው ገደብ እንዲነሳ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠየቁ በባጃጅ ትራንስፖርት ላይ የተሠጠው ውሣኔ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል 2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የህዝብ ንብረት በሙስና ተዘርፏል ሕብረት ባንክ ያሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ ሕብረት ባንክ ያሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ የዘንድሮው የአድዋ በዓልን በምኒልክ አደባባይ ማክበር አለመቻሉ ነዋሪውን አስቆጣ የፀጥታ ኃይሎች በምኒልክ አደባባይ በተሰበሰቡ ነዋሪዎች ላይ ከመጠን ያለፈ እርምጃ ወስደዋል - ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ከትንባሆ ጋር በተያያዘ በዓመት 17 ሺህ ሰዎች ገደማ ይሞታሉ ተባለ ከ800 ሺ በላይ ሰዎች ለአስከፊ ረሃብ ተጋልጠዋል ሰሜን ሸዋ ዞን ተጨማሪ ተፈናቃዮችን መቀበል እንደማይችል ገለፀ ስንዴ በኮንትሮባንድ እየተሸጠ ነው ተባለ በወልቂጤ ከተማ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል በወልቂጤ ከተማ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀ ኢትዮጵያ የመርማሪ ኮሚሽኑ የሥራ ውል እንዲቋረጥ ያቀረበችውን ጥያቄ የአፍሪካ የሰብአዊና ሕዝቦች መብት ኮሚሽን ውድቅ አደረገው በትግራይ ይቋቋማል የተባለው ጊዜያዊ መንግስት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃውሞ ገጠመው ቢጂአይ ኢትዮጵያ፤ ሜታ አቦ ፋብሪካን ለማዘመን ከግማሽ ቢ. ብር በላይ ማውጣቱን አስታወቀ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በንግግር እና ውይይት ተፈታ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ ኮሚቴ ለጠ/ሚ ዐቢይ ጥሪ አቀረበ Videos

የጤፍ ዋጋ ንረቱ ነዋሪውን አስመርሮታል

Addis admass Amharic

3 days 14 hours ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (2)

- ሚኒስቴር መ/ቤቱ የጤፍ ዋጋ መናር አይመለከተኝም ብሏል
- በበርካታ የጤፍ መሸጫ ስፍራዎች የሚሸጥ ጤፍ የለም
- አንድ ኩንታል ጤፍ ከ9ሺ እስከ 10 ሺ ብር እየተሸጠ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ከቀን ወደ ቀን በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመጣው የጤፍ ዋጋ ንረት፣ ነዋሪው ክፉኛ ተማርሯል። በከተማዋ በሚገኙ የጤፍ መሸጫ መጋዘኖችና ወፍጮ ቤቶች ውስጥ ለገበያ የሚቀርብ ጤፍ የለም። ጤፍ ነጋዴዎቹ እንደሚናገሩት ከአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ የሚገባው የጤፍ ምርት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየገባ አይደለም።
በከተማዋ የተለያዩ አከባቢዎች ለጤፍ ሸመታ የወጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት፤ የጤፍ ዋጋ ጭማሪው ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ለመግዛት አልቻሉም። ከቀናት በፊት ከ6000-6500 ይሸጥ የነበረው የጤፍ ምርት፣ በአሁኑ ወቅት ከ9ሺ እስከ 10ሺ ብር ጭማሪ ማሳየቱንና ይህም ከመግዛት አቅማቸው ጋር በፍጹም ሊገናኝ እንደማይችል ተናግረዋል። አሁን ወቅቱ ምርት የተሰበሰበበትና በተሻለ ሁኔታ ለገበያ የሚቀርብበት ቢሆንም፣ የእህል ዋጋ በተለይም የጤፍና የስንዴ ዋጋ እንደ ሰማይ እየራቀ መምጣቱ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚደረገውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር የሚያመለክት ነው ተብሏል።
በዕለት ተዕለት የፍጆታዎች እቃዎች ላይ በህገወጥ መንገድ ጭማሪ በሚያሳዩ ወገኖች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ያለው መንግስት ሰሞኑን እየታየ ባለው የጤፍ ዋጋ ንረት ላይ ምንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ አለመቻሉ ተገቢነት የሌለውና መንግስት ለዜጎቹ ያለውን ቸልተኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉም ነዋሪዎቹ ያማርራሉ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አጠቃላይ የኑሮ ውድነቱን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደማይመለከተው ጉዳዩ ዘርፈ ብዙ ተዋንያን የሚሳተፉበት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አብራርቷል። ዋጋ ባልወጣበት ነገር ላይ ኃላፊነት መውሰድ አይቻልም መባሉም ተዘግቧል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁን ለተፈጠረው የጤፍ ዋጋ ኃላፊነት "ማንዴት" እንደሌለውና የንግድ ሥርዓቱን በተመለከተ በቀጣይ ጥናት አድርጎ ምላሽ ምላሽ እንደሚሰጥ ነው ያስታወቀው።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተጣለው ገደብ እንዲነሳ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጠየቁ

Addis admass Amharic

3 days 14 hours ago

መንግስት ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን ካገደ አንድ ወር ሆኖታል

መንግስት ከየካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለውን ገደብ እንዲያነሳ አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናልእና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) ጠይቀዋል።
ህብረተሰቡ በስፋት በሚጠቀምባቸውና የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በሆኑት ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክ ቶክ እና ዩቲዩብ ላይ መንግስት ክልከላና ገደብ ከጣለ ድፍን አንድ ወር እንደ ሞላው የገለጸው አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል፤ ይህ ድርጊት የዜጎችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና መረጃን የማግኘት መብቶችን በግልጽ የሚጥስ እንደሆነም አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ህገ ወጥ ነው ካለችውና የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖናና ስርዓት የጣሰ ነው በሚል ከእምነቱ ተከታዮች ታላቅ ተቃውሞ ከገጠመው የጵጵስና ሹመትና የሲኖዶስ ምሥረታ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ፣ በመንግሥት የተወሰደው የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን የማገድ እርምጃ ህገ ወጥ መሆኑን ያመለከተው የአሚኒሲቲ መግለጫ፤ ድርጊቱ የአገሪቱን ሕገመንግሥትና የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶች የተቃረነ ነው ብሏል።
በኢትዮጵያ ለዓመታት መጠነ ሰፊ ተቃውሞዎች በሚያጋጥሙበትና በተለያዩ ምክንያቶች ግጭት በሚኖርባቸው አካባቢዎች ኢንተርኔት የማቋረጥና የመዝጋት ተግባር በተደጋጋሚ እንደሚከናወን የተለያዩ ድርጅቶች ሪፖርት አድርገዋል ያለው አምነስቲ፤ ይህ እርምጃም አገሪቱ በሚዲያ ነጻነት ላይ ያላትን አያያዝ የበለጠ የሚያጠለሽ መሆኑን አመልክቷል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በበኩሉ፤ መንግስትበማኅበራዊ የትስስር ገጾች ላይ የጣለው ገደብ “የሰዎችን መረጃ የማግኘትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ገደብ የሚጥል እና የሚጋፋ ስለሆነ” ሊነሳ ይገባል ብሏል። ድርጊቱ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ያመለከተው ኢሰመጉ፤ የመገናኛ ብዙሃን ሥራቸውን በአግባቡ ለሕዝብ እንዳያቀርቡ ችግር በመፍጠር ላይ እንደሆነ አመልክቷል። ገደቡበስራቸው ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠሩ ሳቢያ መንግስት ገደቡን እንዲያነሣ ከዚህ ቀደም በመገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የተጠየቀ መሆኑንም ኢሰመጉ አስታውሷል።
በአገሪቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በተጣለው እገዳ ሳቢያ ተገልጋዮች የትስስር መድረኮቹን ለማግኘት ቪፒኤን የተባሉትን መተግበሪያዎች ለመጠቀም መገደዳቸውን ያመለከተው የሰብአዊ መብቶች ጉባዔ መግለጫ፤ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እነዚህን ማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች በሚያገኙዋቸው ቨርችዋል ፕራይቬት ኔትወርክ ለመጠቀም በመገደዳቸው “የመረጃዎችን የደኅንነት ጉዳይ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል” ብሏል።
ሁለቱ የሠብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማቱ በመግለጫቸው መንግስት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የጣለውን ገደብ በአስቸኳይ እንዲያነሳ እና በቀጣይም በሰዎች ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ እንዲሁም መረጃዎችን የማግኘትና የመቀበል መብት ላይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ አሳስበዋል።
የስታቲስቲክ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ እስከ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ድረስ በኢትዮጵያ በጣም ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ የሆነው ፌስቡክ ወደ 7 ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎች የነበሩት ሲሆን ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት የኢትዮጵያ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ታውቋል።

በባጃጅ ትራንስፖርት ላይ የተሠጠው ውሣኔ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል

Addis admass Amharic

3 days 14 hours ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (3)

• ክልከላውን በሰላማዊ ሰልፍ ባወገዙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ጥይት በመተኮሱ የቆሰሉና የተጎዱ ወጣቶች አሉ
• በመቶዎች የሚቆጠሩ ባጃጆች በክሬን እየተጫኑ ተወስደዋል ተብሏል
• ከ95% በላይ አሽከርካሪዎች የአማራ ተወላጆች በሆኑበት የሥራ ዘርፍ ላይ የተደረገው ክልከላ አማራውን ለማዳከም ከአዲስ አበባ ለማስወጣት ታስቦ በጥናት የተደረገ እንደሆነ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በከተማው የተለያዩ አካባቢዎች አገልግሎት የሚሰጡ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን (በተለምዶ አጠራር ባጃጆች) ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ሥራ መስራት እንደማይችሉ ያሣለፈውን ውሣኔ ተከትሎ ክልከላውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማውገዝና ለተቃውሞ በወጡ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 2 ባለ ባጃጆች መቁሰላቸውና በርካቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።
‹‹የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያ ስራዎችን ለመዘርጋት በሚል ምክንያት የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎትን ላልተወሰነ ጊዜ ያገደው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ፤ የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎቹ ላቀረቡት "የምን ሰርተን እንብላ" ጥያቄ የሠጠው ምላሽ የለም።
በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጋርመንት አካባቢክልከላውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማውገዝናጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ በወጡ ወጣቶች ላይ አድማ በታኝፖሊስ ጥይት በመተኮሱ፣ ሁለት ወጣቶች እንደ ቆሰሉና በርካቶችም ለእስርና ለድብደባ እንደተዳረጉ ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ14 ውስጥ ነዋሪና በባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ስራ የሚተዳደረው ወጣት መስፍን አማረ እንደሚናገረው፣
በአካባቢው በባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ከ5 አመታት በላይ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሶ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማንነታቸው በግልፅ በማይታወቁና በመንግስት ኃይሎች ድጋፍ በሚደረግላቸው ወገኖች የተለያዩ ችግሮች ሲደርስብን ቆይቷል ብሏል። ከ3 ወራት በፊት ባጃጅ በአስፋልት ላይ ማለፍ አይችልም ተብለን ስለተከለከልን ለተወሰኑ ቀናት አስፋልቱ ትተን በኮብልስቶን መንገዶች አገልግሎት መስጠታችንን እንድንቀጥል ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ከቀናት በኋላ ወደ መደበኛው አገልግሎታችን እንድንገባ ተደርጎ፣ ሥራችንን ስንሰራ ቆይተናል ብሏል። አሁን ቢሮው ያሳለፈው ውሣኔ ግን ለሁላችንም ዱብ እዳና ኃላፊነት የማይሰማው ውሣኔ ነው ሲል ተናግሯል።
በህጋዊ ማህበር ተደራጅተው ከጆሞ ወደ መብራት ኃይል፣ ከመብራት ወደ ኃይሌ ጋርመንት፣ ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ሰፈራ፣ ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ሀናማርያም፣ እና ከኃይሌ ጋርመንት ወደ ጋራ በአዲሱ መንገድ ላይ ለአመታት የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን የሚገልፁት የባጃጅ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ለአዲስ አድማስ እንደገለጹት፣ አሁን በድንገትና ምንም ዝግጅት ሳናደረግ ድንገት ስራችሁን መስራት አትችሉም መባላችን እጅግ አስደንግጦናል ብለዋል። "እንዳንሰራ ልንከለከል አይገባንም፣ ምን ሰርተን እንብላ፣ የትእንሂድ!" ያሉት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎችእያንዳንዳችንመተዳደሪያችን በሆነው በዚሁ ስራ አምስትና ስድስት ቤተሰቦች ይዘን በዚህ የኑሮ ውድነት የትውደቁ ልንባል ነው። መንግስት እኛንም እንደዜጋ አይቶን በገዛ አገራችን ሰርተን መኖር እንዳንችል የሚያደርግ ውሣኔውን ዳግም ሊያጤን ይገባል ብለዋል።
የአሠራር ማሻሻያዎች ለማድረግ በሚል ከትራንስፖርት ቢሮው የተሠጠው ምክንያት እውነተኛ አለመሆኑንና መንግስት ከእኛ አውቅና ውጪ በራሱ መንገድ የአካባቢው ነዋሪዎች ያልሆኑና የማይታወቁ ሠዎችን በላያችን ላይ ለማደራጀትና ሌላ ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለማቋቋም ታስቦ ነው ሲሉ ግምትና ጥርጣሬአቸውን ተናግረዋል።
ይህ ባጃጆችን ከስራ የማስቆም ተግባር የተፈጸመው ሰፊ ጥናት ተድርጎ ማንነትን ከለዩ በኋላ ነው የሚሉት እነዚሁ ቅሬታ አቅራቢዎች በዚህ የሥራ ዘርፍ በስፋት ተሠማርቶ የሚገኘው የአንድ ብሔር ተወላጆች በመሆናቸው እነሱን ለማዳከም እና ከአዲስ አበባ ለማስወጣት ሆን ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡
አሁን በአዲስ አበባ የትኛውም አካባቢ ላይ እንዳይሠሩ የተከለከሉት ባጃጆች በተለይ በከተማ ዳርቻ ላይ ባሉ መኖሪያ ሠፈሮችና የጋራ መኖሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሠጡ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በተሽከርካሪዎቹ ላይ የጣለው ክልከላ እስከመቼ እንደሚቆይ ትክክለኛ ቀኑን አላስቀመጠም። በጉዳዩ ላይ ከቢሮው ምላሽ ለማግኘትና ክልከላው እስከ መቼ ድረስ እንደሚቆይ ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ የጸጥታና ደኅንነት ግብረ ኃይል በሰጠው መግለጫ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ 100 ያህል ባጃጆች ባልተፈቀደላቸው አካባቢ አገልግሎት እንሰጣለን በሚል ሁከት ፈጥረው ነበር ብሏል።

2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የህዝብ ንብረት በሙስና ተዘርፏል

Addis admass Amharic

3 days 14 hours ago

• 226ሺ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተብሏል
• 640 የሚሆኑ ሰዎች ከሙስና ጋር የተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸዋል

ባለፈው ህዳር ወር ላይ ለተቋቋመው የብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ በደረሱ ጥቆማዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የህዝብ ንብረት በሙስና መዘረፉ መታወቁን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አስታውቋል፡፡ የክልል ፀረ ሙስና ኮሚቴዎች ባደረጉት ምርመራ ያገኟቸው ውጤቶች ሲጨመሩ ጉዳዩ እጅግ የከፋ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡
በፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ስር የተቋቋሙት የፀረ ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከትናንት በስቲያ በስካይ ላይት ሆቴል ባደረጉት ግምገማና በቀረበው ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው ፤ ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴው ከተለያዩ አካላት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ምርመራ አድረጎ ክስ የመሰረተባቸው ሰዎች 640 መድረሳቸውንና ለተለያዩ ወገኖች ያለ አግባብ ተላልፏል በተባሉ 226ሺ ካሬሜትር ቦታ ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተርና የአስተባባሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፤ ለብሐራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴው የደረሱ ጥቆማዎችን የማጥራትና ተጨባጭ በሆኑ ጥቆማዎች ላይ ምርመራ የማካሄድ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተው ለብሄራዊ ኮሚቴው ከደረሱ 759 ጥቆማዎች በ175 ያህሉ ላይ ምርመራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ በ81 የክስ መዝገቦች በ640 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱንም አመልክተዋል፡፡
2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የመንግስትና የህዝብ ሀብት በሙስና መዘረፉን ያመለከቱት ዳይሬክተሩ ፤ ይህ ቁጥር የክልል መንግስታትና የከተማ አስተዳደሮች ያዋቀሯቸው ኮሚቴዎች በምርመራ ያገኙትን ቁጥር ሲጨምሩበት በከፍተኛ መጠን ሊያድግ እንደሚችልም ገልፀዋል፡፡

(Video) ngo job 12,000$ job vacancy in ethiopia 2022 today | ethio online job vacancy today 2022

ሕብረት ባንክ ያሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ

Addis admass Amharic

3 days 14 hours ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (4)

ቴክኖሎጂው በራሱ ባለሙያዎች አቅም መበልጸጉን አስታውቋል

ሕብረት ባንክ ያሻሻለውን የ*811# ዩኤስኤስዲ ኮድ እና የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ፣ በራሱ የውስጥ ሰራተኞች አቅም በማበልጸግ አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡
ሕብረት ባንክ የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በራሱ የአይቲ ቡድን በመተግበር በሃገራችን የመጀመሪያው ባንክ ነው ተብሏል።
ሕብረት ባንክ የተሻሻለውን የ*811# ዩኤስኤስዲ ኮድ /USSD Code/ እና የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያውን የብሔራዊ ባንክ ተወካይ፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ከትላንት በስቲያ ሐሙስ በባንኩ ዋና መ/ቤት በይፋ አስመርቋል። አዲሱ የሕብረት ሞባይል ባንኪንግ፤ የባንኩን ገጽታ በጠበቀ መልኩ የተለያዩ ዘመናዊ አገልግሎቶችን አካትቶ፣ ለደንበኞች አጠቃቀም ምቹና ፈጣን በሆነ ሁኔታ ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑ ነው የተገለጸው።
የተሻሻለውን “የሕብር ሞባይል አገልግሎት” አስመልክቶ የሕብር ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ፣ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ረፋዱ ላይ በባንኩ ዋና መ/ቤት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳብራሩት፤ የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ሁለት ነገሮች ልዩ ያደርጉታል። የመጀመሪያው በውስጡ በርካታ አገልግሎቶችን ያካተተ መሆኑ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ በራስ የውስጥ ባለሙያዎች አቅም መበልጸጉ ነው፤ ብለዋል።
ይህም በዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ለሌሎች ባንኮችና ለሀገር አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን በመወከል የተገኙት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት ክትትልና ልማት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ዳምጠው በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዲጂታል የክፍያ ሥርዓትን ለማሻሻልና የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ባንኮችም በዚሁ ሥራ ላይ በመሳተፋቸው በዲጂታል የክፍያ አገልግሎት አሰጣጥ እድገት እየታየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
“ፕሮጀክቱ በራስ አቅም መሰራቱ የውጭ ምንዛሬን ከማዳኑም ባሻገር ባንኩ ወደፊት ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ለሚያከናውናቸው የሲስተም ኢንተግሬሽን ሥራዎች ጠንካራ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ሀገራችን ለምትከተለው የብሔራዊ ዲጂታይዜሽን ስትራቴጂ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው።” ብሏል፤ ባንኩ ባወጣው መግለጫ።
በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ በራስ አቅም ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ተጠቃሽ የሆነው ሕብረት ባንክ ከዚህ ቀደምም የኮር ባንኪንግ ሥርዓቱን በሀገራችን የባንክ ዘርፍ ባልተለመደ ሁኔታ በራሱ የውስጥ አቅም ማሻሻሉን በመግለጫው አስታውሶ፤ በተጨማሪም በኦንላይን ባንኪንግ፣ በዳታ ሴንተርና በዲዛስተር ሪከቨሪ ፋሲሊቲ የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ማኔጅመንት ሲስተም ISO/IEC 27001:2013 መስፈርትን በማሟላት፣ አስተማማኝ የደህንነት ስርዓት በመዘርጋትና ሰርቲፋይድ በመሆን በሀገራችን የቀዳሚነቱን ቦታ የያዘ ባንክ መሆኑን አውስቷል፡፡

Administrator

ሕብረት ባንክ ያሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ

Addis admass Amharic

3 days 14 hours ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (5)

የዘንድሮው የአድዋ በዓልን በምኒልክ አደባባይ ማክበር አለመቻሉ ነዋሪውን አስቆጣ

Addis admass Amharic

1 week 4 days ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (6)

• በዓሉን ለማክበር የወጣ አንድ መምህር በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል
• በርካቶች በፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል
• የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ በአስለቃሽ ጭስ ተስተጓጉሏል
• በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በርካታ ህጻናትና አቅመ ደካሞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል
• ቤተክርስቲያኗ በጉዳዩ ላይ መግለጫ ታወጣለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ላለፉት 127 ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ምኒሊክ አደባባይ በታላቅ ድምቀት ሲከበር የኖረው የአድዋ ድል በዓል፤ ዘንድሮ ከፍተኛ ችግር ገጥሞታል፡፡ በዓሉን ለማክበር በስፍራው በተሰባሰበው ነዋሪ ላይ የፀጥታ ሀይሎች በወሰዱት የሃይል እርምጃ፣ የሰው ህይወት ማለፉንና በርካታ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡
በየዓመቱ የካቲት 23 የሚከበረው የአድዋ ድል በዓል ቀድም ሲልም ሲከበርበት በቆየው የሚኒሊክ አደባባይ ላይ ለማክበር የሚሄዱ ሰዎችን የፀጥታ ሃይሎች ወደ ስፍራው የሚወስዱትን አምስት መግቢያ መንገዶች በመዝጋት፣ በዓሉን ለማክበር ወደ አደባባዩ የሚሄደውንም ሆነ ዓመታዊውን የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ንግስ ለማክበር ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄደውን ምዕመን በመኪናም ሆነ በእግር እንዳያልፍ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ከጎጃም በረንዳ ወደ ሚኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብቻ ነበር ለእግረኛ ክፍት የተደረገው።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ማለዳ ላይ በዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው ከሄዱ በኋላ ወደ አደባባዩ በመጠጋት ፎቶግራፍ ለመነሳትና በተለያዩ መንገዶች በዓሉን ለማክበር የሚፈልጉ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሰዎች በስፍራው ተሰብስበው ነበር፡፡ የፀጥታ ሀያሎች በስፍራው በዓሉን ማክበር እንደማይቻል በመግለጽ የተሰበሰበውን ሰው ለመበተን በተኮሱት አስለቃሽ ጭስ፣ የላስቲክ ጥይትና እውነተኛ ጥይት በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጋቸው የታወቀ ሲሆን በዓሉን ለመታደም ከስፍራው የነበረ አንድ መምህር ከፀጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉም ተነግሯል፡፡
የዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሲቪክ መምህር እንደነበር የተነገረው መምህር ሚሊዮን ወዳጅ፤ ሚኒሊክ አደባባይ አካባቢ ከፀጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተመቶ ወዲያውኑ ህይወቱ ማለፉ ተናግሯል፡፡ ሚሊዮን በጥይት በተመታበት ቅፅበት ሕይወቱ ያለፈ ቢሆንም፤ ወደ አብንት ሆስፒታል እንዲሄድ ተደርጓል፡፡
በሆስፒታሉ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች እንደገለፁትም ሚሊዮን የተመታበት ጥይት በአንድ ጎኑ ገብቶ በሌላኛው እንደወጣና ህይወቱም ወዲያውኑ እንዳለፈ ተናግረዋል፡፡
የፀጥታ ሃይሎች በአደባባዩ ላይ የነበረውን ህዝብ በአስለቃሽ ጭስና ጥይት ለመበተን ከሞከሩም በኋላ በመናገሻ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል በማክበር ላይ የሚገኙ ምዕመናን ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱንና በዚህ ሳቢያም የንግስ ክብረ በዓሉ መቋረጡን በርካታ ህፃናትና አቅመ ደካማ ምዕመናን ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታውቋል፡፡ በምዕመናኑ ላይ በደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ሳቢያ ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ መደረጉንም ሀገረ ስብከቱ አስታውቋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ቤተክርስቲያኒቷ ወቅታዊ መግለጫ ትሰጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅም ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)፤ የአድዋ በዓልን በሚሊኒክ አደባባይ ለማክበር ወጥቶ ከፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ማለፉ የተነገረውን ወጣት መምህር ሚሊዮን ወዳጅን አሟሟት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ ወጣቱ የፓርቲው አባል እንደነበር አስታውሶ፤ በሰላማዊ መንገድ የአድዋ በዓልን ለማክበር በወጣበት ሁኔታ በሚሊኒክ አደባባይ በፀጥታ ሀይሎች በግፍ ተገድሏል ብሏል፡፡
የፀጥታ ሀይሎች በበዓሉ አክባሪዎች ላይ ከፈፀሙት ድርጊት ጋር በተያያዘ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ አብን በመግለጫው ጠይቋል፡፡
የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በዓሉ በታሰበው ሁኔታ መከበሩን አመልክቶ፤ አንዳንድ ሰዎች በሚኒሊክ አደባባይና በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቀጽር ግቢ በተሰበሰበው ህዝብ ላይ ረብሻ ለመቀስቀስ መሞከራቸውንና ይህንን ለመቆጣጠር መንግስት በወሰደው እርምጃም በምዕመናን ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።
በሚኒሊክ አደባባይ የነበረውን ግርግርና የጸጥታ ሃይሎች በዓሉን ለማክበር በተሰባሰበው ህዝብ ላይ የወሰዱትን የብተና እርምጃ በስፍራው ተገኝተን ለመመልከት እንደቻልነው፣ የጸጥታ ሃይሎች በሚኒልክ አደባባይ ላይ በመሰባሰብ በዓሉን ለማክበርና በመቀጠልም ወደ አድዋ ድልድይ ለመሄድ የሞከሩ በርካታ የበዓል አክባሪዎችን አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ በትነዋል። በዚህ ሳቢያም በተፈጠረ ረብሻና ግርግር በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ተጎጂዎችም በአቅራቢያ ወደሚገኙ የጤና ተቋማት ተወስደዋል። የፀጥታ ሃይሎች በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አመታዊውን ክብረ በዓል በማክበር ላይ በነበሩ ምዕመናንና በርካታ ህፃናትና አቅመደካማ ምዕመናን ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። በጉዳቱ ራሳቸውን የሳቱ ምእመናን በአንቡላንስ ወደተለያዩ የህክምና ተቋማት ተወስደዋል። በሌላ በኩል 127ኛው አድዋ በዓል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችና ዝግጅቶች በመስቀል አደባባይ ተከብሯል።

የፀጥታ ኃይሎች በምኒልክ አደባባይ በተሰበሰቡ ነዋሪዎች ላይ ከመጠን ያለፈ እርምጃ ወስደዋል - ኢሰመኮ

Addis admass Amharic

1 week 4 days ago

(Video) አስቂኝ ፕራንክ😂 #viral #viralshorts #viralvideo #shorts #prank #funnyshorts 2023

ኢትዮጵያ ቅኝ ገዥውን የጣሊያን ጦር ድል የነሳችበትን ዓመታዊውን የዓድዋ ድል በዓል ለመታደም በምኒልክ አደባባይ በተሰበሰቡ ነዋሪዎች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች አላስፈላጊና ከፍተኛ ሃይል መጠቀማቸውንና በዚህም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ/ አስታወቀ።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በሰላማዊው ህዝብ ላይ ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ የፕላስቲክና እውነተኛ ጥይቶችን መተኮሳቸውንም ኢሰመኮ ትናንት ባወጣው መግለጫ አመልክቶ።
ከትላንት በስቲያ ሐሙስ በምኒልክ አደባባይ የዓድዋ ድል በዓልን ለማክበር በተሰባሰቡ ነዋሪዎች እንዲሁም በቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የንግስና በዓል እያከበሩ በነበሩ ሰዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች፣ በኃይል አላስፈላጊ እና ከመጠን ያለፈ እርምጃ መውሰዳቸውን ኢሰመኮ ገልጿል።
በምኒልክ አደባባይ ዋናው ዝግጅት ላይ ሕዝቡ እንዳይታደም ወደ አደባባዩ የሚወስዱት መንገዶች ተዘግተው እንደነበርና እንዳይተላለፍም በፀጥታ ኃይሎች ታግዶ እንደነበር ያመለከተው መግለጫው፤ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በህዝቡ ላይ ከልክ ያለፈ እርምጃ መውሰዳቸውን ጠቁሟል። በመንግስት በተወሰደው አላስፈላጊና ከልክ ያለፈ እርምጃ ሳቢያ በርካታ ሰዎች በእድሜ የገፉና ሕፃናትም ጭምር ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል ብሏል። በዚህም ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት እንደተቀጠፈና፣ በበርካቶችም ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን አመልክቷል። በተጨማሪም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ አባሉ እንደሆነ የገለጸው ሚሊዮን ወዳጅ የዓድዋ ድል በዓልን ለማክበር ወጥቶ ከመንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ መገደሉን ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የፀጥታ ኃይሎች የሕዝብን ደኅንነት መጠበቅና የሁሉንም ሰው ሰብዓዊ መብቶች ማስጠበቅ ቀዳሚ ኃላፊነታቸው መሆን ነበረበት ያለው ኢሰመኮ፤ ሕዝቡ በተለምዶ በየአመቱ እንደሚያደርገው ምኒልክ አደባባይ እንዲሁም በአቅራቢያው በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በዓሉን ለማክበር በሰላማዊ መልኩ ተሰባስቦ እንደነበርና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ከልክ ያለፈ እርምጃ እንደተወሰደበት አመልክቷል።
ድርጊቱን የፈጸሙ የፀጥታ ኃይል አባላት ሊጠየቁ እንደሚገባ ያስታወሰው መግለጫው፤ “የሕግ አስከባሪዎች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ በበቂ ሁኔታ ሥልጠና ሊሰጣቸው ይገባልም”ብሏል።

በኢትዮጵያ ከትንባሆ ጋር በተያያዘ በዓመት 17 ሺህ ሰዎች ገደማ ይሞታሉ ተባለ

Addis admass Amharic

1 week 4 days ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (7)

የምግብና መድሀኒት ባለሥልጣን አዲስ ድረ-ገፅ ይፋ አደረገ

በኢትዮጵያ የትንባሆ አጠቃቀም ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሳምንት 259 ወንዶችና 65 ሴቶች እንዲሁም በዓመት 16 ሺህ 800 ሰዎች እንደሚሞቱ ተገለፀ፡፡
ይህንን የገለፀው የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ባለፈው ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል አዲስ ድረ-ገፅ ባስተዋወቀበት ወቅት ነው፡፡
ባለስልጣኑ መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔን ለማጠናከር ከዴቨሎፕመንት ጌትዌይ ጋር በመተባበር፣ የኢትዮጵያ ትንባሆ ቁጥጥር ድረ-ገፅን (Ethiopia.tobaccontroldata.org) እ.ኤ.አ ከ2021 ዓ.ም ጀምሮ ሲያዘጋጅ መቆየቱን የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ዋና የዳይሬክተር ሔራ ገርባ ተናግረዋል።
ድረ-ገፁ በዋናነት ህግ አውጪዎችና ውሳኔ ሰጪ አካላት ትንባሆ ቁጥጥርን በሚመለከት የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውንም አይነት መረጃዎች በአመቺ ሁኔታ እንዲያገኙ ለማድረግ መዘጋጀቱንም ዋና ዳይሬክተሯ ጨምረው ተናግረዋል። እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ፤ በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ድረ-ገጹ ውጪ የደቡብ አፍሪካ፣ የዛምቢያና የናይጀሪያ ድረገጾች ተዘጋጅተው ጥቅም ላይ ውለዋል። በቀጣይ የኬንያና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ድረ-ገጾች ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ የተባለ ሲሆን፣ እነዚህ ድረ-ገጾች የተዘጋጁት ዴቨሎፕመንት ጌትዌይ ሚለንዳጌትስ ፋውንዴሽን ባደረገለት የገንዘብ ድጋፍ በሚያስፈጽመው የትምባሆ ቁጥጥር ዳታ ኢኒሼቲቭ (TCDI) ፕሮግራም አማካኝነት ነው ተብሏል።
ዋና ዳይሬክተሯ ጥናቶችን ጠቅሰው እንደተናገሩት፤ በዓለም ዙሪያ የትምባሆ ፍጆታ እየቀነሰ ቢሆንም በአፍሪካ ግን ከፍተኛ የአጫሾች ቁጥር ጭማሪ ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆሙ ሲሆን በተለይ በኢትዮጵያ እስካሁንም ድረስ ሲጋራዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኙ በመሆናቸው ጉዳዩን አሳሳቢ እንዳደረገው በአጽንኦት ገልጸዋል።
በሀገራችን ብዙ ወጣቶች መኖራቸውና የገቢ መጠናቸው እየጨመረ መሄድ፣ በትምባሆ አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን በተመለከተ የግንዛቤ ውስንነት፣ የትምባሆ ቁጥጥር ፖሊሲዎች እንዳይጸድቁና ተግባራዊ እንዳይሆኑ የትምባሆ ኢንዱስትሪው ጣልቃ ገብነትና ተያያዥ ጉዳዮች ለአጫሾች ቁጥር መጨመር በምክንያትነትና በስጋትነት ተጠቅሰዋል።
በዚህም ምክንያት ከ15 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው 3.4 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የትምባሆ ምርቶችን ይጠቀማሉ የተባሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ በአፍሪካ ውስጥ ካሉትና በጣም ጠንካራ ከሚባሉት የቁጥጥር ህጐች የሚመደብ ቢሆንም፣ አተገባበሩ ግን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።

ከ800 ሺ በላይ ሰዎች ለአስከፊ ረሃብ ተጋልጠዋል

Addis admass Amharic

2 weeks 4 days ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (8)

“ረሃቡ ከቀጠለ ቦረና ምድረ በዳ ትሆናለች”

በደቡብ ኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የተከሰተው ድርቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርብቶ አደሮችን ለአስከፊ ረሃብ ማጋለጡ ተጠቁሟል። በዞኑ ከሚገኙ አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊየን ነዋሪዎች መካከል ከስምንት መቶ ሺ በላይ የሚሆኑት የድርቁ ሰለባ ሆነዋል። ድርቁ ሶስት ሚሊዮን የሚደርሱ የቀንድና የጋማ ከብቶችን የገደለ ሲሆን በዚህምወደ 30 ቢሊየን ብር የሚገመት ሃብትን አሣጥቷል ተብሏል።
በዞኑ የገጠር መንደሮች የሚገኙ ነዋሪዎች መንደራቸውን ለቀው ወደ ከተሞች በመሰደድ ላይ ሲሆኑ፤ድርቁ እጅግ ያዳከማቸውና በእድሜ የገፉ ሰዎች ግን ረሃቡን መቋቋም አቅቷቸው እየሞቱ መሆኑ ታውቋል። የቦረና ዞን የተልተሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጎንጎ ዋሪዮ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ በወረዳው በተከሰተው ረሃብ እስካሁን የሁለት ወር ህጻንን ጨምሮ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል።
መንግሥት በዞኑ በድርቅ ሣቢያ ለረሀብ የተጋለጡ ወገኖችንለመታደግ አላስፈላጊ የፖለቲካ ሽኩቻዎችና መጠላለፎችን ወደ ጎን ትቶ፤ ለረሀብ ለተጋለጡ ወገኖቻችን ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሠራ ኢዜማ ጠይቋል።
ከተጋረጠው ሰብዓዊ ቀውስ አንፃር መንግስት አስቸኳይ ብሔራዊ የዕርዳታ ኮሚቴ አቋቁሞና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተባብሮ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ሊደርስላቸው እንደሚገባም ኢዜማ ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
በዞኑ በታልታሌ ወረዳ ቡሌደንቢ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት አርብቶ አደር ማሌኖ ታራ ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት፤ በዞኑ ላለፉት አምስት የዝናብ ወቅት በጠፋው ዝናብ ሣቢያ መሬቱ ዘር ለማብቀል የሚችል ባይሆንም፣ አርብቶ አደሩባለው መሬት ላይ ዘር እየበተነ ሲጠባበቅ ጠብ የሚል ነገር በማጣቱ ለከፋ ረሃብ ተዳርጓል። “አርብቶ አደሩ ለአመታት በዘለቀው ድርቅ ሣቢያ ጥሪቱን አሟጦ ጨርሶ ባዶ እጁን ቀርቷል። መሬቱ ደርቋል፤ እህል አያበቅልም። ከብቶቻችን በረሃብና ጥም አልቀዋል። ቀረን የምንለው ነገር የለም፡፡ ያልተራበ ማንም የለም። በርካታ ሰዎች ቀናትን ያለ ምግብና ውሃ በማሳለፍ ላይ ናቸው፤ ረሃቡ ከብቶቻችንን ጨርሶ ፊቱን ወደ እኛ አዙሯል። መንግስት ረስቶናል ወገኖቻችንም ጨክነውብናል ፈጣሪም ፊቱን አዙሮብናል።” ብለዋል፤ አርብቶ አደሩ።
ትንሽ አቅም ያለውና ረሃቡ ክፉኛ ያልጎዳው እግሩ ወደመራው ተሰዷል።ቀደም ያሉት እንደውም ከሞት የተራረፉ ከብቶቻቸውን ይዘው ነው የተሰደዱት። አሁን ሰዉም ከብቱም መንከላወስ አቅቶታል መንግስትና ወገን እንዲደርስልን ከመማጸን በስተቀር ምንም ማድረግ አንችልም” ብለዋል።
አርብቶአደር ማሊኖን ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የቦረና ነዋሪዎችና አርብቶ አደሮች በተራዘመው ድርቅ ሳቢያ አሁን አቅማቸው ተንኮታኩቷል፡፡ በዞኑ ከፍቶ በቀጠለው ድርቅ የተፈተነው አርብቶአደርለከፋ ረሃብ ተጋልጧል። አስራ ሶስቱም የዞኑ ወረዳዎች የድርቁ ሰለባዎች ሆነዋል። በዞኑ ከሚገኙ አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊየን ነዋሪዎች ስምንት መቶ ሺ ያህሉ የድርቁ ሰለባ መሆናቸው ተገልጿል።
የቦረና አርብቶአደር የኑሮ መሠረት ከሆኑት ከብቶች 3 ሚሊዮን የሚሆኑት በዚሁ ድርቅ ሣቢያ አልቀዋል።
ከዚህ በፊት በዞኑ ከፊል ወረዳዎች በድርቅ ሲመቱአርብቶ አደሩ የራሱንና የከብቶቹን ህይወትለማትረፍ ወደ አጎራባች ወረዳዎች ይሰደድ እንደነበር የሚገልጹት በዞኑ የአሬሮ ነዋሪና የመንግስት ሠራተኛ የሆኑት አቶ ታምሩ ጉልማ፤አሁን ግን ሁሉም የዞኑ ወረዳዎች በድርቁ ክፉኛ በመጠቃታቸውማህበረሰቡ የሚሰደድበት ስፍራ አጥቷል ብለዋል፡፡ ከወራት በፊትቁጥራቸው ቀላል የማይባል የቦረና አርብቶ አደሮች ድርቁንና አስከፊውን ረሃብ በመሸሽ ወደ አርሲና ጂንካ ከብቶቻቸውን ይዘው መሠደዳቸውንም ገልጸዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ ለቀናት ከእህልና ውሃ ተነጥሎ በመክረሙ አቅሙ ከድቶታል። ከብቶቹን ትቶ ህይወቱን ለማትረፍ እየተጣጣረ ነው ያሉት አቶ ታምሩ፤ “ከራሱ በፊት ለከብቶቹ ህይወት ቅድሚያ ይሰጥ የነበረው የቦረና አርብቶ አደር፣ የጎጆውን መሸፈኛ ሣር ሣይቀር ለከብቶቹ ሰጥቶ ሊያተርፋቸው ባለመቻሉ አይኑ እያየ ከብቶቹን ረሃቡ ነጥቆታል። አሁን የራሱንም ህይወት ለማትረፍ የሚያስችል አቅም አጥቷል።
“በዚህች ደቂቃ እንኳን በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ማህበረሰብ በረሃብና ረሃቡን ተከትሎ በሚመጡ በሽታዎቸ እየሞቱ ነው። በቦረና ታሪክ እንዲህ አይነት አስከፊ ረሃብ ታይቶ አያውቅም። መንግስት በቸልተኝነቱ ከቀጠለና ህዝቡን ከረሃብና ሞት መታደግ ካልተቻለ አካባቢው በጥቂት ጊዜ ምድረበዳ መሆኑ አይቀሬ ነው” ሲሉ መጪውን አስከፊ ሁኔታ ገልጸውታል። በቤት አንስሳቱና በቀንድ ከብቶቹ ላይ የከፋ እልቂትን ሲያስከትል የቆየው ረሃብ ወደ ዱር እንስሳትም መዛመቱ አሳሳቢ ነው አስብሏል። ድርቁ እልቂቱን ያስከተለው በሁሉም አይነት የእንስሳት ዝርያ ላይ ነው፡፡ ድርቅና በረሃን ይቋቋማሉ የሚባሉ እንደ ግመል ያሉ እንስሳትም በዚህ ድርቅ እየረገፉ መሆኑን ያመለከተው ከዞኑ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ከቤት እንስሳት በተጨማሪም አሁን አሁን የዱር እንስሳትም ድርቁን መቋቋም ተስኗቸው በስፋት እያለቁ መሆኑን አመልክቷል። በቦረና ፓርክ በጥበቃ ውስጥ የሚገኙ የዱር እንስሳትም ጭምር የረሃቡ ሰለባ እየሆኑ መሆኑን የገለጸው መረጃው በፓርኩ የከፋ የውሃ እጥረት በማጋጠሙ በዱር እንስሳቱም ላይ ሞት እየተከሰተ መሆኑን አመልክቷል።
ከ40 ዓመታት ወዲህ ተከስቶ አያውቅም የተባለው በዚህ የቦረና ድርቅና ረሃብ ሣቢያ ለአስከፊ ሞት የተጋለጡ ወገኖችን ለመታደግ ከመንግስት በተጨማሪ መንግስታዊ ያልኾኑ ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የዕርዳታ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት፣ አክቲቪስቶች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶችና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ኢዜማ በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።
“የፓርቲያችን አባላትም በያላችሁበት አካባቢ ኹሉ ወገኖቻችንን ለመታደግ በሚደረጉ ሰብዓዊና ወገናዊ ዘመቻዎች ላይ የተለመደውን ግንባር ቀደም ተሳትፏችሁን እንድታከናውኑ እናሳስባለን።” ብሏል ኢዜማ፡፡
የቀጠናው የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የአየር ትንበያ ማዕከል ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት፤ የአፍሪካ ቀንድ ከዚህ በፊት ከታየው የከፋ ቸነፈር ገጥሞታል ብሏል። በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያና ኬንያ በአሁኑ ወቅት የሚታየው የድርቅ ሁኔታ ሩብ ሚሊዮን ሰዎችን ከገደለውና ከ 12 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም ከታየው የባሰ እንደሆነም አመልክቷል።

ሰሜን ሸዋ ዞን ተጨማሪ ተፈናቃዮችን መቀበል እንደማይችል ገለፀ

Addis admass Amharic

2 weeks 4 days ago

- ባለፉት 2 ዓመታት 72 ሺህ ተፈናቃዮችን ተቀብለናል
-ባለፉት 10 ቀናት ብቻ ከኦሮሚያና ከአዲስ አበባ ብቻ 9 ሺህ ተፈናቃዮች ወደ ዞኑ መጥተዋል

የተፈናቃይ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱና በሀብት እጥረት ሳቢያ ተጨማሪ ተፈናቃዮችን መቀበል እንደማይችል የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ\ቤት አስታወቀ፡፡
ጽ\ቤቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለይ በዞኑ በተከሰቱ ተደጋጋሚ ግጭቶችና ጦርነቶች እንዲሁም ከኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ ብቻ የመጡ ከ77 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን በብዙ ተግዳሮት እስከዛሬ ይዞ መቆየቱን ጠቁሞ፤ ከፌደራል መንግስት የሚመጣው ድጋፍ በቂና የተሟላ ፓኬጅ ካለመሆኑ በተጨማሪ በየወሩ ስለማይመጣ የዞኑ አመራርና የፅ\ቤቱ ሰራተኞች ህብረተሰቡን በማስቸገር በግል ውስን ለጋሶችን በመለመን ተፈናቃዮችን እንዳይሞቱ እንዳይድኑ ሆነው እንዲኖሩ ሲታገል መቆየቱን አመልክቷል።
የዞኑ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ\ቤት ሀላፊ አቶ አበባው መሰለ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት ባለፉት አስር ቀናት ብቻ ከአዲስ አበባና ከምስራቅ ወለጋ ከባኮ ዞን አኖ አካባቢ የመጡ ወደ 3ሺህ ተፈናቃዮችን፣ የተቀበሉ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተካሄደ ባለው የቤት ፈረሳ ምክንያት ወደ 6 ሺህ በድምሩ 9 ሺህ ተፈናቃዮች ተቀብለዋል፡፡
“እኛ ተፈናቃይ ስንቀበል ሁሉን አቀፍ የሆነ ድጋፍ ነው የሚጠበቅብን” ያሉት ሀላፊው፤ እስካሁን መጠለያ፣ አልባሳት ቀለብ፣ ህክምናና መድሀኒት እያቀረብንና ብዙ ተግዳሮቶችን ተጋፍጠን ብንቆይም ለተጨማሪ ተፈናቃዮች ግን ይህን ሁሉ የማሟላት አቅም የለንም ብለዋል።
የዞኑ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ደብረ ብርሃን ከተማን ጨምሮ በዞኑ ያሉ 31 ወረዳዎችን እንደማስተዳደሩ፣ በተለይ በሰሜን ሸዋ አጣዬና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በተደጋጋሚ በሚፈጠር ችግር ብዙ ተፈናቃይ ስላለ፣ የመጠለያ ችግር ከመከሰቱ የተነሳ በደብረ ብርሃንም ተፈናቃዮች በባለሃብቶች ፋብሪካዎች ውስጥ ነው የተጠለሉት ያሉት ሃላፊው፤ ይህ ቁጥር ይቀንሳል ብለን ስንጠብቅ እያደር መጨመሩ በእጅጉ አስጨንቆናል ብለዋል፤ ለአዲስ አድማስ።
“እኛ ተጨማሪ ተፈናቃይ አንቀበልም ያልነው ወገኖቻችንን ጠልተን ሳይሆን ከፍተኛ የሀብት ችግር ስላለብን ነው” ያሉት አቶ አበባው፤ “እዚህ መጥተው አይናችን እያየ በረሀብ እንዲሞቱ አንፈልግም” ብለዋል።
እስካሁንም ያሉት ሁሉ ተሟልቶላቸው እየኖሩ እንዳልሆነ የተናገሩት ሃላፊው፤ የዞኑና የደብረ ብርሃን አመራር እየተሯሯጠ ህብረተሰቡም ከልጆቹ ጉሮሮ እየነጠቀና እየሰጠ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውንና ባለሃብቶች ፋብሪካዎቻቸውን ለመጠለያነት ሰጥተው ባለፉት ሁለት ዓመታት ስራ ፈትተው መቀመጣቸውን አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ሆነ የኦሮሚያ ክልል ችግር ሲፈጠርና ህዝብ ሲፈናቀል መፍትሄ እስኪመጣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ሰብስቦ በመያዝና አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መቆየት እንዳለበት የገለጹት ሃላፊው፤ “እየመጣ ባለው የተፈናቃይ ቁጥር በእጅጉ ተጨናንቀናል፤ እስከመቼስ ነው የምንቀበለው፤ ምን ያህል ተፈናቃይ ስንቀበል ነው የሚቆመው” ሲሉ ጠይቀዋል።
“ሀገር በተለያየ ችግር በተወጠረችበት በዚህ ሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 10 እና 15 ዓመት የኖሩ ዜጎችን ቤት እያፈረሰ ማፈናቀል የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲሉ የጠየቁት አቶ አበባው፤ ቤት ማፍረሱ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነም ከተማ አስተዳደሩ ላፈናቀላቸው ዜጎች መፍትሄ መፈለግ አለበት ብለዋል።
እንደ አቶ አበባው ገለጻ፤ በዞኑ የተለያየ ችግር ደርሶባቸው እርዳታ የሚፈልጉ 546 ሺህ ሰዎች መኖራቸውንና 135ሺህ ህዝብ ደግሞ የሴፍቲኔት ተጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ ከክልሉ ውጪ ማለትም ከኦሮሚያና ከአዲስ አበባ የተቀበልናቸው ተፈናቃዮች ግን 85 ሺህ ደርሰዋል፤ እስካሁን ተፈናቃዮቹ በደብረብርሃን፣ በምንጃር ሸንኮራ፣ በሚዳወረሞ፣ በመርሃቤቴ፣ በእንሳሮ፣ በመንዝ ማማ፣ በመንዝ ላሎ እና በተለያዩ ቦታዎች ተጠልለው እንደሚገኙ በመጠቆም፣ “በዚህ የተነሳ ነው ሌሎች ተፈናቃዮችን መቀበል ያልቻልነው” ሲሉ አቶ አበባው አስረድተዋል።

ስንዴ በኮንትሮባንድ እየተሸጠ ነው ተባለ

Addis admass Amharic

2 weeks 4 days ago

- የአንድ ኩንታል ስንዴ ዋጋ ሰባት ሺ ብር ደርሷል
- በስንዴ ዋጋ መናር ሳቢያ ዳቦ ቤቶች ስራቸውን እያቆሙ ነው
- አርሶ አደሩ አንድ ኩንታል ስንዴ በ3200 ብር ለመንግስት እንዲያስረክብ ይገደዳል

መንግስት የስንዴ ምርትን ወደ ውጪ አገር መላክ መጀመሩን ተከትሎ፣ የስንዴ ዋጋ በከፍተኛ መጠን እየናረ ሲሆን በአዲስ አበባ የአንድ ኩንታል ስንዴ ዋጋ 7ሺ ብር መድረሱ ታውቋል።
የስንዴ ዋጋ ንረቱ የተፈጠረው መንግስት የስንዴ ምርትን ወደ ውጪ አገር መላክ መጀመሩን ይፋ ካደረገ በኋላ ሲሆን፤ ይህም በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ የዳቦ መጋገሪያ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ጫናን መፍጠሩ ተነግሯል። የዋጋ ንረቱ ከአቅማችን በላይ ነው ያሉት የዳቦ መጋገሪያ ድርጅቶች ባለንብረቶች፤ ሥራውን ለማቆም መገደዳቸውን ይገልጻሉ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አውቶቡስ መናኸሪያ አካባቢ የሚገኘው የነሂማ ዳቦ መጋገሪያ ባለቤት አቶ ከድር ሙክታር እንደሚሉት፤ በስንዴ ምርት አቅርቦት እጦት ሳቢያ የዳቦ መጋገር ስራቸው ለቀናት የተስተጓጎለ ሲሆን ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ የዳቦ መጋገሪያ ድርጅታቸውን ለመዝጋት እንደሚገደዱ ተናግረዋል።
“በህገወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ ነጋዴዎች የሚሸጠውን ዱቄት በሰባትና ስምንት ሺ ብር እየገዛን ዳቦ ጋግረን ለመሸጥ ስለማንችል፣ ያለን አማራጭ ስራችንን ማቆም ብቻ ነው” ብለዋል።
እንደ አቶ ከድር ሁሉ የስንዴ ዋጋ ንረቱ በርካታ የዳቦ መጋገሪያ ድርጅቶችን ስራ ያስተጓጎለ ሲሆን በሂደቱም ድርጅታቸው እንዲዘጋ የሚያስገድዳቸው መሆኑን ይናገራሉ። በስንዴ ዋጋ መናር ሳቢያ የተፈጠረው የዳቦ ምርት እጥረት በምግብ ሸቀጦች ዋጋ ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል ተጠቁሟል።
መንግስት በዚህ አመት ለውጪ ገበያ ከሚቀርበው ስንዴ 150 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም፣ ይህ የመንግስት ዕቅድ ገና ከጅምሩ የአገር ውስጥ ገበያውን ማናጋት ጀምሯል ተብሏል።
መንግስት የኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ ስንዴ አብቃይ በሆኑ ክልሎች ያሉ አርሶ አደሮች፣ ለውጪ ገበያ የሚቀርብን ስንዴ በአነስተኛ ዋጋ ለመንግስት አንዲያቀርቡ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። በዚህ የመንግስት አዲሱ መመሪያ መሰረትም፤ አርሶአደሩ አንዱን ኩንታል ስንዴ በ3200 ብር ሂሳብ ለህብረት ስራ ማህበራት እንዲያስረክብ ታዝዟል። ይህ ሁኔታ ያልተዋጠላቸው አርሶአደሮች በተጠቀሰው ዋጋ መሸጥ አያዋጣንም በማለት ምርቱን ለመሸሸግና ለኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ለመሸጥ መገደዳቸውን ለማወቅ ተችሏል። የስንዴ ምርትን ሸሽገው የተገኙ አሊያም በህገወጥ መንገድ ከቦታ ወደ ቦታ ሲያዘዋውሩ የተገኙ አርሶአደሮችም ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቃቸውና ምርቱም እንደሚወረስ አዲሱ መመሪያ ያመለክታል።
ስንዴ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ለማህበረሰቡ የሚሸጠው የስንዴ ምርት በኩንታል ከ4ሺ እስከ 5ሺ ብር የሚደርስ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ኩንታል ስንዴ ከ7ሺ እስከ 7ሺ አምስት መቶ ብር እየተሸጠ ይገኛል። ይህም የሆነው ገበያው ከስንዴ አምራች አካባቢዎች እየራቀ በሄደ ቁጥር የኬላ ክፍያውም እየጨመረ ስለሚሄድ እንደሆነ ነጋዴዎች ይናገራሉ።
መንግስት ወደ ውጪ ለመላክ ካቀደው የስንዴ ምርት ውስጥ 3.1 ሚሊዮን ኩንታል ድርሻው የኦሮሚያ ክልል ሲሆን፤ ክልሉ የተጣለበትን ኮታ ለማሟላት አርሶ አደሮች የስንዴ ምርታቸውን በርካሽ ዋጋ እንዲሸጡለት እያግባባ ነው ተብሏል።
ክልሉ ኮታውን ለማሟላት ስንዴ አብቃይ ለሆኑ ዞኖች ኮታ አከፋፍሎ፣ ዞኖች በወረዳዎች አማካኝነት የተመደበባቸውን የስንዴ ኮታ እንዲሰበስቡ የማድረጉን ተግባር እንደተያያዙት ታውቋል። አርሶ አደሮቹ ባለፉት አመታት አንድ ኩንታል ማዳበሪያ በ1500 ብር ሂሳብ እየገዙ፣ የሚያመርቱትን ስንዴ ኩንታሉን በ4ሺ ብር ሲሸጡ መቆየታቸውን ጠቅሰው፤ አሁን የአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ዋጋ ወደ 4500 ብር ባሻቀበበት ወቅት ያመረቱትን የስንዴ ምርት በ3200 ብር ሽጡ መባላቸው ፈጽሞ ተገቢነት የለውም ሲሉ መቃወማቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።
በተፈጠረው የዋጋ ውዝግብ ሳቢያ በአካባቢዎቹ ስንዴን እንደ ልብ ለገበያ አቅርቦ መሸጥ እንዳልተቻለና በርካታ አርሶ አደሮችም የስንዴ ምርትን በቤታቸው ሸሽገዋል በሚል ምክንያት የቤት ለቤት ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በአሁኑ ወቅት በስንዴ ዋጋ ላይ እየታየ ያለው ከፍተኛ ጭማሪ እየቀጠለ እንደሚሄድ ግምታቸውን የገለጹት ምንጮች፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የታየው የዋጋ ጭማሪ ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር እስከ 2000 ብር ጭማሪ ማሳየቱንም ጠቁመዋል።

(Video) #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #ethiopian_orthodox_tewahedo🇪🇹 #habeshatiktok #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በወልቂጤ ከተማ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል

Addis admass Amharic

3 weeks 4 days ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (9)

- ከ30 ሰዎች በላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል
- ግድያው ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው እርምጃ ነው - ኢሰመኮ

የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልቂጤ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች የቧንቧ ውሃ አቅርቦት ለረዥም ጊዜ መቋረጡን ተከትሎ፣ መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ባለፈው ረቡዕ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ሰልፍ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በመንግስት ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት የሞቱ ነዋሪዎች ቁጥር 6 መድረሱን ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ ተናገሩ፡፡
ከግጭቱ ጋር በተያያዘም፣ ከትላንት ጀምሮ ትራንስፖርትን ጨምሮ ሁሉም አይነት አገልግሎቶች መቋረጣቸውን፤ የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
በወልቂጤ ከተማ የውሃ ችግር ከሰባት ዓመት በላይ የዘለቀና ነዋሪውን ሲያሰቃይ የነበረ ጉዳይ ቢሆንም በተለይ ባለፉት አምስት ወራት ግን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ዉሃ መጥፋቱንና ህዝቡ ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጉን ነው ነዋሪዎች ለአዲስ አድማስ የተናገሩት።
በከተማው ውስጥ ቀደም ባለው ጊዜ የነበረው የውሃ አገልግሎት በማስተላለፊያ መስመሮች እድሳት እጦት፣ በከተማው ነዋሪ ቁጥር ማደግ እንዲሁም በፍላጎት መጨመር ሳቢያ ፍላጎትና አቅርቦት ሊመጣጠን አለመቻሉን የገለፁት ነዋሪዎቹ፤ ከዚህ በተጨማሪም ውሃው ባለበት በቋሚነት አገልግሎት መስጠቱን እንዳይቀጥል ሌላም እንቅፋት እንደገጠመው አስረድተዋል።
ወልቂጤ ከተማ ውሃ የምታገኝበትና በቸሃ ወረዳ የሚገኘው ”ቡዠባር” የውሃ ሳይት ቀቤና ወረዳና ቸሀ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ 10 ያህል ቀበሌዎች ውሃውን ለመስኖና ለሽያጭ በማዋላቸው ወደ ወልቂጤ የሚፈሰውን ውሃ እንዲቀንስ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ እንዲጠፉ ማድረጋቸውን የገለፁት ነዋሪዎች፤ ይህ ችግር በተለይ ላለፉት አምስት ወራት በቋሚነት በመቀጠሉ ህዝቡን በብሶት ወደ አደባባይ እንዳስወጣው ተናግረዋል።
የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የአይን እማኝ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፣ የከተማዋ የውሃ ችግር እየተባባሰ የመጣው ከአራት አመት ወዲህ ቢሆንም፣ ከዚያም በፊት ባለው ጊዜ ህዝቡ ውሃ የሚያገኘው በፈረቃና በሳምንት አንድ ጊዜ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ከአምስት ወር በፊት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ውሃ መቋረጡንና በወር ከ15 ቀን (በ45 ቀናት) አንድ ጊዜ እሱም ሰው በተኛበት ሌሊት በአሳቻ ሰዓት እንደሚለቀቅ የጠቆሙት የአይን እማኙ፤ ይህ በ45 ቀን በለሊት የሚለቀቅ ውሃ አብዛኛው ነዋሪ በተኛበት ለሁለት ሰዓታት መጥቶ ስለሚጠፋ፣ ሰው ውሃ ለማግኘት ሌላ 45 ቀናት ለመጠበቅ እንደሚገደድ ተናግረዋል።
የወልቂጤ ህዝብ ይህን የውሃ ችግርና ስቃይ መቋቋም ስላልቻለ ወደ ወልቂጤ የሚመጣውን ውሃ ጠልፈው ለሽያጭ ከሚያውሉ ቀበሌዎች ለመግዛትና ህይወቱን ለማቆየት በባጃጅ በጋሪና በተለያየ አማራጮች ሩቅ መንገድ እየተጓዘ፣ አንድ ጀሪካን ውሃ በ20 ብር እየገዛ ችግሩን ለመቋቋም ሲታገል መቆየቱን ነው የአይን እማኙ የተናገሩት፡፡
በአሁን ወቅት የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ከ150 ሺህ በላይ መድረሱን የገለፁት የአይን እማኙ፤ ይህ የውሃ እጦት ስቃይ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የ150 ሺህ ህዝብ ስቃይ መሆኑንም በምሬት ተናግረዋል፡፡ ህዝቡ ይህ ብሶቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ባለፈው ረቡዕ የውሃ መቅጃ ጀሪካኑን እየያዘ ወደ ከተማዋ የውሃ ልማት መስሪያ ቤት በማቅናት ችግሩን ገልፆ ሀላፊዎች መልስ እንዲሰጡ ቢጠባበቅም፣ ከመስሪያ ቤቱ ሀላፊዎች አንድም ጉዳዩን ነገሬ ብሎ ለህዝቡ ጥያቄ መልስ የሚሰጥ በመጥፋቱና ጥያቄና ጩኸት እየጨመረ በመምጣቱ፣ የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ወደ ቦታው መድረሱን ነዋሪው ተናግረዋል፡፡
የከተማው ፖሊሶች ጉዳዩ የውሃ ችግር ጥያቄና ሰላማዊ መሆኑን ካዩ በኋላ፣ ፖሊሶችም የችግሩ ተጠቂ በመሆናቸውና የህዝቡ ጥያቄ ተገቢ ነው ብለው በማመናቸው ወደ መጡበት መመለሳቸውን ማየታቸውን ነዋሪው ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል።
“በተለይ ባለፉት አምስት ወራት ህዝቡ እንዲህ አይነት የውሃ እጥረት ችግር ውስጥ ሲገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት፤ የዞኑና የከተማው የውሃ ልማት መስሪያ ቤት ሀላፊዎች ችግሩን ለመቅረፍ ለምን ጥረት አላደረጉም” በሚል የተጠየቁት ነዋሪው ሲመልሱ፤ “እስካሁን ለአንድ ክፍለ ከተማ በቂ ነው በሚል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ጀምረው ነበር፤ ይህ በጣጢሳ ቀበሌ የተጀመረው “ጣጢሳ የውሃ ሳይት” በሁለት ወር ውስጥ ተመርቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ሀላፊዎች ቃል ቢገቡም፤ ቆፋሮው ከተጀመረ ሰባት ወራት አልፎት ለከተማው ነዋሪ ጠብ ያለለት ውሃ እንደሌለ ነው በምሬት የገለጹት፡፡
“የከተማው ሀላፊዎች በማህበራዊ ሚድያ ችግሩ ሲነገርና ህዝቡ ሲማረር የተለመደ ግን መፍትሄ የማያመጣ መግለጫ ያወጣሉ “ያሉት ነዋሪው፤ “መፍትሄ ሊመጣ ነው፣ ችግሩን ለመፍታት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ርብርብ ላይ ነን፤ እንዲህ እያደረግን ነው፤ እንዲያ እየሰራን ነው ከማለት ውጪ በተጨባጭ የሰሩት ነገር የለም። ይህንንም የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን የፌስቡክ ገፅ ላይ ገብቶ ከመቼና መቼ ጀምሮ ይህንን መግለጫ ያወጡ እንደነበር መመልከት ይቻላል ብለዋል፡፡
ህዝቡ ለከተማ አስተዳደሩ ሀላፊዎች እንደምክረ ሃሳብ ሲያቀርብ የነበረው “ሩቅ ቦታ አትሂዱ፤ ወልቂጤ ከተማ ሰፊ የውሃ ክምችት አላት፤ 3 ሜትር ተቆፍሮ ውሃ ማግኘት የሚቻልባትና በክልሉም በውሃ ሀብቷ ቀዳሚ ናት፤ ለምን እሩቅ ቦታ ትሄዳላችሁ” በማለት ነበር ያሉት ነዋሪው፤ ሰሚ በማጣት አሁን ግን ችግሩ ብሶበት በሰላም ችግሩን ለመግለፅ አደባባይ የወጣ ነዋሪ በጥይት እየተመታና እየቆሰለ ነው ሲሉ በምሬት ተናግረዋል፡፡
በሰላማዊ ሰልፉ ዕለት የተፈጠረውን ነገር ባይናቸው እንዳዩ የተናገሩት የአይን እማኝ፤ ሰልፉ ሆን ተብሎ፣ አስተባባሪ ኖሮት የተጠራ ሳይሆን ሰው ውሃ ልማት በር ላይ ሄዶ የሚያናግረው ሲያጣ ቁጥሩ እየጨመረ መጥቶ፣ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ መቀየሩን አስታውሰው፤ ምንም ሌላ አላማ የሌለውና፣ ህዝቡ ከውሃ መቅጃ ጄሪካን ውጪ የያዘው ነገር እንዳልነበረ ጠቁመዋል።
ይህን የተመለከቱት የከተማው የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊና የልዩ ሀይል ሀላፊው በህዝቡና በፀጥታ ሰራዊቱ መካከል በመቆም “እናንተ ኮሚቴ መርጣችሁ ስጡንና ወደየቤታችሁ ግቡ፤ እኛ ከመረጣችኋቸው ኮሚቴዎች ጋር ተነጋግረን ለችግራችሁ አፋጣኝ መፍትሄ እንሰጣለን “በማለት ህዝቡን ለመበተን ቢሞክሩም፣ ህዝቡ ደግሞ “እስከዛሬ ኮሚቴ እየመረጥን እየላክን ብንቆይም እነዚያ ኮሚቴዎች በሚያስፈራሯቸው አካላት እየፈሩና እየተደለሉ የህዝብን ጥያቄ እየረሱ ለዚህ ችግር በቅተናል፤ እኛ የምንፈልገው የሚመለከታቸው የዞኑ አስተዳዳሪ፣ የውሃ ልማት ሃላፊውም ሆነ ከንቲባው እዚህ መጥተው፣ በዚህ በዚህ ቀን ችግራችሁ ይፈታል፤ በዚህ ችግር ምክንያት ነው እስካሁን የተቸገራችሁት ብለው እንዲያስረዱን ነው” ሲሉ መግለጻቸውን ነው የአይን እማኙ የተናገሩት።
ከዚያ በኋላ ወደ ቤት ግቡ አንገባም በሚል ጭቅጭቅ፣ “ውሃ እንፈልጋለን፣ ውሃ ተጠምተናል፣ ሃላፊዎቹ ቀርበው ምላሽ ይስጡን” በሚል ህዝቡ ድምፁን ሲያሰማ የከተማው ጻጥታ ዘርፍ ሃላፊና የልዩ ሃይል አዛዡ ወደ ህዝቡ አስለቃሽ ጭስና መሳሪያ እንዲተኮስ ትዕዛዝ መተላለፉን በቦታው ሆነው መስማታቸውንና ማየታቸውን የአይን እማኙ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል።
ተኩሱን ተከትሎም፤ ግንባራቸውን፣ ደረታቸውን፣ ሆዳቸውን ተመትተው የሞቱ፣ አጥንታቸው የተሰበረና የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ነዋሪው፤ ከሞቱት 6 ሰዎች አራቱን እንደሚያውቋቸው ተናግረዋል።
ሆስፒታል ውስጥ አንድ አስጊ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው እንዳለ፣ አንዱ በቀዶ ህክምና ጥይት እንደወጣለት፣ የአጥንት ስብራት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ያሉና ታክመው የተመለሱ መኖራቸውንም አክለው ገልፀዋል- እማኙ።
“ከጉራጌ ክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሰልፎች ተደረጉ ቢሆንም፤ አሁን የተከሰተው ግን ከቀድሞው ጋር ፈጽሞ እንደማይገናኝ ነው የአይን እማኙ ያስረዱት።
ወደ ወልቂጤ ሪፈራል ሆስፒታል ደውለን ከሀኪሞች እንዳረጋገጥነው ከሆነ፤ ረቡዕ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በተከሰተው በዚሁ ግጭት ወደ ሆስፒታሉ 17 ተጎጂዎች ገብተው የነበረ ሲሆን፣ ሁለቱ ወጣቶች በእጅጉ ተጎድተው ሆስፒታል ሲደርሱ ወዲያው ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። “ከ17ቱ መካከል 3ቱ በጠና ታመዋል” ያሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሆስፒታሉ ሃኪም፤ አንዱ ዕድሜው ወደ 60 የሚጠጋና መንገደኛ የነበረ ሲሆን ጭንቅላቱን በልዩ ሃይል ተመትቶ፤ ግማሹ የፊቱ ክፍል፣ ጥርሱና የመተንፈሻ አካሉ በእጅጉ መጎዳቱንና ብዙ ደም የፈሰሰው መሆኑን አስረድተዋል። “ሌላው ወጣት ደግሞ ደረቱ ላይ ተመትቶ መተንፈስ ሁሉ የከበደውና በኦክስጅን ሀይል ያለ ሲሆን ደም በብዛት ፈስሶት አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል” ያሉት የህክምና ባለሙያው፤ ሌላው ወጣት ሆዱ ላይ ተመትቶ በርካታ ደም የፈሰሰው መሆኑንና የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል።
“እንዴት አገርንና ህዝብን ለመጠበቅ የሰለጠነ ዘመናዊ የጸጥታ ሃይል፣ በሰለጠነ ዘመን ወንድሞቹ ላይ አልሞ ይተኩሳል” ያሉት ሃኪሙ፤ “ወደ ሆስፒታል የመጡት ተጎጂዎች በሙሉ ግንባራቸውን፣ ሆዳቸውን፣ ደረታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ሌሎች የአጥንት ክፍሎቻቸውን በኢላማ የተመቱ ናቸው። ይህ በጣም አሳዝኖኛል” ብለዋል።
እንደ ሃኪሙ ገለጻም፤ በጠና ከታመሙት ውጪ ያሉት 12ቱ ታካሚዎች፤ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸውም በተለያየ መልኩ እየታከሙና የጤና መሻሻል እያሳዩ ነው።
“ከሆስፒታላችን ውጪ ሦስት ሰዎች በቦታው ላይ መሞታቸውን አውቃለሁ። አንዱ ከወላይታ፣ አንዱ ከጎንደር ለስራ የመጡ ወጣቶች ሲሆኑ አንደኛው የከተማው ነዋሪ ነው” ያሉት የህክምና ባለሙያው፤ በተጨባጭ አምስት ሰዎች መሞታቸውን እንደሚያውቁና ገና ቤተሰባቸው ያልተገኙ፣ በደንብ ያልታወቁ ሟቾች ሊኖሩ እንደሚችሉ ግምታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፤ በከተማው በሚገኙ ሁለት የጤና ጣቢያዎች እንደዚሁ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ተጎጂዎች እንዳሉና ጤና ጣቢያዎቹ ማከም በሚችሉት ደረጃ የሚሰፋውን ሰፍተው የሚፈስ ደም አስቁመው እያከሟቸው ያሉ ተጎጂዎችም እንዳሉ፣ ሃኪሙ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል።
የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ አሰፋና የከተማው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ትዕግስቱ ፉጂን በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን ደጋግመን በእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ምላሽ ባለማግኘታችን ሃሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትላንት ባወጣው መግለጫ፤ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በውሃ ችግር ምክንያት መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ለማቅረብ ሰልፍ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በፀጥታ ሃይሎች በተወሰደ የሃይል እርምጃ፤ በነዋሪዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቁሞ፤ የአይን እማኞችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችንና የጤና ባለሙያዎችን በማነጋገር ባሰባሰበው መረጃና ማስረጃ፣ ሶስት ሰዎች ጭንቅላታቸውንና ደረታቸውን በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ማረጋገጡን ያመለከተ ሲሆን፤ ቢያንስ ከ30 ሰዎች በላይ የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፤ የተወሰደው የሃይል እርምጃ ከነገሩ መነሻና ሁኔታ አንጻር ሲታይ ተመጣጣኝ አለመሆኑን ገልጸው፣ “አንገብጋቢ በሆነው የውሃ አቅርቦት ጥያቄ ሰልፍ ወጥተው ድንጋይ በወረወሩና መንገድ በዘጉ ሰዎች ላይ ህይወት የሚያጠፋ መሳሪያ ተጠቅሞና ጥይት ተኩሶ ነዋሪዎችን መግደል ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እርምጃ ነው” ብለዋል።
አክለውም፤ መንግስት አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጥና ለተጎጂዎች ተገቢውን ካሳ ሊከፍል እንደሚገባ አሳስበዋል። ለወደፊትም ተመሳሳይ የመብት ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ለጸጥታ ሀይሎች ግልጽ አመራር እንዲተላለፍ አሳስበዋል-ኮሚሽነሩ።

በወልቂጤ ከተማ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል

Addis admass Amharic

3 weeks 4 days ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (10)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአመራሮቹ አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ አፀደቀ

Addis admass Amharic

3 weeks 4 days ago

• የጥቅማጥቅም ክፍያው በወር ከ5,800 ብር እስከ 15,200 ብር ይደርሳል
• የጥቅማጥቅም መመሪያው ቤት ለሌላቸው አመራሮች ቤት መሰጠትን ይ ጨምራል
• በከተማው ክፍለ ከተሞች ውስጥ ያሉ ከስራ አስፈጻሚ እስከ ቡድን መሪ ድረስ የጥቅማ ጥቅሙ ተካፋዮች ናቸው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ከከፍተኛ አመራር እስከ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚዎችና የቡድን መሪዎች ያሉ አመራሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዲስ የጥቅማጥቅም መመሪያ አፀደቀ። መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ መ/ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ከአመራር ውጪ ያሉ ሰራተኞችን አይመለከትም ተብሏል።
ይኸው ሰሞኑን የፀደቀውና በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ቢሮዎች፣ ኤጀንሲዎች፣ ክፍለ ከተማና ወረዳ ውስጥ ያሉ አመራሮችን ያጠቃልላል የተባለው አዲስ መመሪያ፤ ቤት ለሌላቸው አመራሮች ቤት መስጠትን፣ ከታክስ ነፃ የሆኑ ክፍያዎችን፣ ቤት ላላቸው አመራሮች የቤት እድሳት ወጪን መሸፈን እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማቅረብን ያካትታል።
በገንዘብ ተሰልቶ የሚከፈለውና ከታክስ ነጻ ሆኖ በተለያየ እርከን ላይ ላሉ አመራሮች የሚሰጠው ጥቅማጥቅም፤ ከፍተኛው በወር 15 ሺ 200 ብር እንዲሁም ዝቅተኛው 5800 ብር ሲሆን ይህም ከደመወዛቸው ውጪ የሚሰጥ እንደሆነም ታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ሰሞኑን ያጻደቀውና በከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ተቋማት ውስጥ ያሉ አመራሮችን ተጠቃሚ በሚያደርገው በዚህ አዲስ መመሪያ ላይ አመራሮች የማይመለስ ላቶፕ ኮምፒውተርና ሞባይል ስልክ ማግኘት የሚያስችላቸው እንደሆነም ተገልጿል።
በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ አስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ውስጥ ያሉ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ ስራ አስፈጻሚዎች እስከ ቡድን መሪ ድረስ ያሉ አመራሮች እንዲሁም የየወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊዎች ጭምር የአዲሱ መመሪያ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል። ይህ አዲሱ የጥቅማጥቅም መመሪያ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ መ/ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ከአመራር ውጪ ያሉ ሰራኞችን አይመለከትም ተብሏል።

ኢትዮጵያ የመርማሪ ኮሚሽኑ የሥራ ውል እንዲቋረጥ ያቀረበችውን ጥያቄ የአፍሪካ የሰብአዊና ሕዝቦች መብት ኮሚሽን ውድቅ አደረገው

Addis admass Amharic

3 weeks 4 days ago

የስራ ውል የማቋረጡ ጥያቄ በቅርቡ ለሚካሔደው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ይቀርባል ተብሎ ነበር

የፌደራሉ መንግስት ከህውኃት ኃይሎች ጋር ባደረገው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምር የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የባለሞያዎች ኮሚሽን የሥራ ውል እንዲቋረጥ በኢትዮጵያ የቀረበውን ጥያቄ፤ የአፍሪካ የሰብአዊና ሕዝቦች መብት ኮሚሽን ውድቅ አደረገው። የስራ ውል እንዲቋረጥ የቀረበው ጥያቄ በቅርቡ ለሚካሄሔደው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባኤ እንደሚቀርብ ተገልጾ ነበር።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሰሜን ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ዓመታት በተደረገው ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር መነሳቱና መርማሪ ኮሚሽን ማቋቋሙ ተገቢ አለመሆኑን የገለጸችው ኢትዮጵያ፤ ድርጊቱ ባለፈው ጥቅምት ወር ከተፈረመው የሰላም ሥምምነት ወዲህ የታዩ መሻሻሎችን እንደሚያስተጓጉል አስታውቃለች።
ከትላት በስቲያ የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በተጀመረው የአፍሪካ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ጥያቄው በቅርቡ ለሚካሔደው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት እንደሚቀርብም ተናግረዋል፡፡
“በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የተደረሰው የሰላም ሥምምነት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማምጣት የሚለውን መርሃ ያንጸባረቀ ነው” ያሉት አቶ ደመቀ፤
“በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መፍትሄ ለመፈለግ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን፣ አይዘነጋም። በአፍሪካ ኅብረት የተመራውን የሠላም ሂደትና በፕሪቶሪያ የተፈጸመውን የሠላም ሥምምነት በመርዛማ ትርክት የሚበክልና በአገሪቱ ተቋማት እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያዳክም ነው “ ሲሉ መናገራቸው ይታወሣል።
ይህንኑም ተከትሎ የአፍሪካ የሰብአዊና ሕዝቦች መብት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሬሚ ንጎይ ሉምቡ፤ ኮሚሽኑ እያከናወነ የሚገኘው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የማጣራት ሥራውን እንደሚቀጥልና ምርምራውንም እያጠናቀቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በተመድ የተቋቋመው ኮሚሽን ባለፈው መስከረም ባወጣው የመጀመሪያ ሪፖርት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመፈጸማቸው ማስረጃ እንዳገኘ ያስታወቀ ሲሆን፤ መንግሥት የኮሚሽኑን ሪፖርት ተአማኒነት የሌለው ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል፡፡
ሦስት አባላት ያሉት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜኑ ጦርነት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን እንዲመረምር የተቋቋመው አለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን፣ በኢትዮጵያ ኤርትራና ህወሓት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር ጥሰት ፈጻሚዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

በትግራይ ይቋቋማል የተባለው ጊዜያዊ መንግስት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃውሞ ገጠመው

Addis admass Amharic

3 weeks 4 days ago

(Video) ethiopian ልዩነቲን ያጣጥሙት 🥰 funny video 2022

ከሁለት ዓመታት በላይ በጦርነት ውስጥ የዘለቀችው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መንግስት ለማቋቋም እየሰራ መሆኑንና ጊዜያዊ መንግስቱ የሚመሰረትበት ሰነድም በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ የተሰጠውን መግለጫ ተከትሎ፣ በክልሉ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ፓርቲዎቹም በሰጡት በዚሁ መግለጫም፤ በትግራይ ክልል መሰረታዊ የተባለውን ጊዜያዊውን ክልላዊ መንግስት ከሚያቋቁመው ኮሚቴ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው በመጥቀስ፤ኮሚቴውን አንቀበልም ብለዋል፡፡
“ኮሚቴው ለህወኃት የሚያደላና ገለልተኛ ያልሆነ ኮሚቴ ነው፤ ህወኃት የክልሉ መንግስት ሆኖ ይቀጥላል፡፡ የሚቀየር ነገር የለም” ብለዋል- ተቃዋሚዎቹ፡፡
በክልሉ ይመሰረታል የተባለውን ጊዜያዊ ክልላዊ መንግስት ለመመስረት እንዲያስችል የተቋቋመውና በሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ሊቀመንበርነት የሚመራው ኮሚቴ፣ በክልሉ ጊዜያዊ መንግስት ለማቋቋም የሚያስችል የምስረታ ሰነድ በቀጣዩ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርጉና በዚህ ጉዳይ ላይ በክልሉ ውስጥ ከሚገኘው ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከነዋሪው ህዝብ ጋር ዛሬና ነገ ሰፊ ውይይት ሊደረግ መታሰቡን ተገልጾ ነበር። ይህንን መግለጫ ተከትሎ በክልል ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኑት ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ፣ ብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ ባይቶና እና ውደብ ነፃነት ትግራይ የተባሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትላንት በጋራ በሰጡት መግለጫ ጊዜያዊ መንግስት ለመመስረት የተቋቋመውን ኮሚቴ እንደማያውቁና እንደማይቀበሉ ተናግረዋል። ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በሰጡት በዚሁ መግለጫ፤ የውድብ ነጻነት ትግራይ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ደጀን መዝገበ እንደተናገሩት፤ “የጊዜያዊ መንግስት መስራች ኮሚቴውን ህወኃትና ሰራዊቱ አዋቅረውታል ምንም የሚመጣ ለውጥ የለም፤ ተቃውሞ ግን ይቀጥላል” ብለዋል፡፡
ውጥ በማናመጣበት ጉዳይ ውስጥ መግባት እስፈላጊነቱ አልታየንም ያሉት ዶ/ር ደጀን፤ ኮሚቴው ለህወሃት የሚያደላ ነው የገለጹት። ብለው እንደሚያምኑ የገለፁት ዶ/ር ደጀን መዝገበ በዚህ ኮሚቴ የሚዋቀር ጊዜያዊ ክልላዊ መንግስት ለውጥ ሊያመጣ አይችልም ብለዋል፡፡
የሳልሳይ ወያኔ ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ክንፈ ሀዱሽ በበኩላቸው፤ ኮሚቴው የተደራጀበት መንገድ ግልፅ ያለመሆኑን ጠቁመው፣ “ለአንድ አካል የሚወግን ነው ብለን ስለምናምን ከኮሚቴው ጋራ ምንም ዓይነት ግንኙነት አይኖረንም፡፡ ለራሱ ህልውና የሌለው አካል ጊዜያዊ አስተዳደር ለመመስረት የሚያስችል ኮሚቴ መሆን የለበትም” ሲሉም ተቃውመዋል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በክልሉን የሚቋቋመው ጊዜያዊ መንግስት የክልሊን ህዝብ ፍላጎት መሰረት ያደረገና ሁሉንም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በእኩልነት ያካተተ እንደሚሆን ነው የገለጹት፡፡

ቢጂአይ ኢትዮጵያ፤ ሜታ አቦ ፋብሪካን ለማዘመን ከግማሽ ቢ. ብር በላይ ማውጣቱን አስታወቀ

Addis admass Amharic

3 weeks 6 days ago

Addis admass Amharic | ETHIO ADDIS LINK (11)

ቢጂአይ ኢትዮጵያ የሜታ አቦ ፋብሪካን እንደገና ለማደስና ለማስፋፋት ከ550 ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱን አስታወቀ፡፡
በዛሬው ዕለት የካቲት 9 ቀን 2015 ዓ.ም በሰበታ ከተማ በሜታ አቦ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀ ሥነሥርዓት ላይ የቢጂአይ
ኢዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄርቬ ሚልሃድ፣ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ሥራዎችን በሚመለከት አጭር መግለጫ ለባለድርሻ
አካላት አቅርበዋል፡፡
የቢጂአይ የሥራ እንቅስቃሴዎች በአራት ዘርፎች ላይ ያተኮረ መሆኑን በመግለጫው የጠቆመው ኩባንያው፤ እነሱም የሰው ኃይል፣
የማምረት አቅም ግንባታ፣ ሽያጭና ሥርጭት እንዲሁም ማህበራዊ ሃላፊነት ናቸው ብሏል፡፡
አዲሱ የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ባደረጉት ንግግር፤ ቢጂአይ የሜታ አቦ ፋብሪካን አቅም ለማሳደግ፣ ስሙን ለማደስና
ኩባንያውን ለመንከባከብ እንዲሁም ከሰበታ ከተማ ህዝብ፣ ከአካባቢው አስተዳደርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የጠበቀ ግንኙነት
ለመፍጠር የገባውን ቃል አስታውሰዋል፡፡
"የገባነውን ቃል በትክክል እንደፈጸምን ለመግለጽ በመቻሌ ደስታ ይሰማኛል" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህን አባባላቸውን
ለመደገፍ የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር፣ ቢጂአይ ያከናወነውን ሥራ በጥልቀት ከገመገመ በኋላ፣ በጥር ወር 2015
ዓ.ም የሰጠውን ውህደትን የመፈጸም ፍቃድ በማስረጃነት ጠቅሰዋል፡፡
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜታ አቦን በወር 300ሺ ሄክቶ ሊትር ለማምረት የሚችልና ከቢጂአይ ቤተሰብ ድርጅቶች ውስጥ ትልቁ የቢራ
ፋብሪካ ለማድረግ አቅዶ መነሳቱን የጠቆመው መግለጫው፤ ለዚህም ሦስት ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም
ያለው ትልቅ ጀኔሬተር ግዢን ጨምሮ በዘመናዊ ማምረቻ መሣሪያዎች ግዢ ላይ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ ላይ እንደሚገኝ
አመልክቷል፡፡
ቢጂአይ የምርት ሽያጭና ሥርጭቱን ለማስፋፋት በሚያደርገው ጥረት በተመረጡ ገበያዎች ላይ የሚያተኩረውን ሥልቱን በመከተል
ውጤታም ሥራ ለመሥራት በመቻሉ፣ በአሁኑ ወቅት የሜታ ምርቶች ፍላጎት ከአቅርቦት በላይ ሆኖ መገኘቱም ተጠቅሷል፡፡

Administrator

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ ኮሚቴ ለጠ/ሚ ዐቢይ ጥሪ አቀረበ

Addis admass Amharic

1 month ago

ኮሚቴው በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍና መከራ በአስቸኳይ ይቁም ሲል ጠይቋል።
- በሚሊዮን የሚቆጠር የኢትዮጵያ ህዝብ በመንግስት ላይ ያለው እምነት እየተሸረሸረ መሆኑን ኮሚቴው አመልክቷል። - ችግሩ በአፋጣኝ ካልተፈታ አገሪቷ በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቅ ቀውስ ውስጥ ትገባለች ብሏል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያውያ ጉዳይ ኮሚቴ (ኢፓክ) ከዓለም አብያተክርስቲያናት፣ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ካውንስል፣ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል፣ ከምስራቅና ኦረየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እና ከበርካታ ታዋቂ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበራትና ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ጋር በመሆን በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ እንዲያስቆሙና አገሪቱን ከቁልቁለት ጉዞ እንዲመልሱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ።
በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለተፈጠረው ቀውስ መነሻ ምክንያቶቹ በህገ-ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያፈነገጡት ቡድኖች መሆናቸው በግልጽ እየታወቀ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሃይሎች የበርካታ ንፁሃንን ህይወት ሲቀጥፉ ቤተክርስቲያኒቱ ክብሯ ሲዋረድና ከባድ ውድመት ሲደርስባት መንግሰት ሁኔታውን በዝምታ መመልከቱ በእጅጉ አስገርሞናል ያለው ኮሚቴው ይህም መንግስት የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ሃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣቱን አመላካች ነው ብለዋል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ዲያስፖራው በመንግስት ላይ ያለው እምነት በፍጥነት እየተሸረሸረ ሄዷል ያለው ኮሚቴው መንግስት ቀውሱን ለመፍታት ያለው ፍላጎት አነስተኛ መሆኑ ቀውሱን እራሱ አውቆ የፈጠረውና የሚደግፈው ነው ብሎ ለማመን የሚያስገድድ ሁኔታ ላይ እንዲደረስ ማድረጉን አመልክቷል።
በአገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ እና የህግ ጥሰት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ካውንስል ለፌደራል መንግስትና ለተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ለመገናኛ ብዙሃን አካላት ያስተላፈውን መልዕክት በመደገፍ ተቋማቱ ሃላፊነት የሞላበትንና ህጋዊ አካሄድ በተከተለ መንገድ መፍትሄ ለመሻት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ አካላት በቤተክርስቲኗ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና በደል አጥብቆ እንደሚቃወም የገለጸው ኮሚቴው በቅዱስ ሲኖዶሱ የተመደቡ የሃይማኖት መሪዋችን ማሰር መደብደብና ማጉላላት፣ ወደሀገረ ስብከታቸው እንዳይገቡ መከልከል፣ ምዕመናንን በጭካኔ መግደል፣ ያፈነገጡትንና በቅዱስ ሲኖዶሱ የተወገዙትን ሊቃነጳጳሳት በመደገፍ ህግ በመጣስ የአብያተክርስቲናትን በር እየሰበሩ ማስገባት፣ የቤተክርስቲኒቱን ክብር ማጉደፍና ሀብትና ንብረቷን የማዘረፍ ወንጀል አጥብቀን እንቃወማለን ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህገ-መንግስቱና ለሀገሪቱ ህግ የበላይ ጠባቂ መሆናቸውን በመገንዘብ ሃላፊነት ተሰምቷቸው አቅጣጫቸውን እንዲያስተካክሉና አገሪቱን ከከፋ መቅሰፍት እንዲያድኑ ጥሪ ያቀረበው ኮሚቴው ችግሩ በቶሎ ካልተፈታና እየተባባሰ ከሄደ ሀገሪቷ ከዚህ ቀደም በታሪኳ ካጋጠሟት ሁሉ የከፋ ቀውስ እንደሚያጋጥማትና መውጫ የማይገኝለት አዙሪት ውስጥ እንደምትገባ አበክሮ አሳስቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱ በድንገት ከገባችበት ቀውስ ውስጥ ለማዳን የሚያስችል ትክክለኛና ቆራጥ አመራር እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

Administrator

Subscribe to Addis admass Amharic feed

catagory

Amharic news

(Video) dire 🥹#yutinass #ethiopian_tik_tok #ethiopian #ethiopia

Videos

1. Technology Career path in Amharic Language Part 3
(yayobe Yoseph)
2. አስቂኝ ፕራንክ😂 #viral #viralshorts #viralvideo #shorts #prank #funnyshorts
( mentaochu)
3. የቲክቶኳ ንግስት ethiopian tiktok #dinklejoch #ethiopiantiktok #ethiopiannews 2023
(BRIGHT SIDE ለማመን የሚከብድ ድንቃ ድንቅ ትእይንቶች)
4. 🔴New 2022 Ethiopian Club live mix #Non stop[,#YARED_NEGU,#JOB27,#DAVIDO,#KIZZ_DANIEL
(Dj Alew)
5. All Leaders R 👑 Except That እባብ #ethiopia #orthodox
(ethiopia prank stars)
6. ሀዲይሳ መዝሙር ዘማሪ ABDINAGO GADISA #EXCITED BY THIS #SONG
(SARE WANA ሀዲያ )
Top Articles
Latest Posts
Article information

Author: Melvina Ondricka

Last Updated: 03/29/2023

Views: 6355

Rating: 4.8 / 5 (68 voted)

Reviews: 83% of readers found this page helpful

Author information

Name: Melvina Ondricka

Birthday: 2000-12-23

Address: Suite 382 139 Shaniqua Locks, Paulaborough, UT 90498

Phone: +636383657021

Job: Dynamic Government Specialist

Hobby: Kite flying, Watching movies, Knitting, Model building, Reading, Wood carving, Paintball

Introduction: My name is Melvina Ondricka, I am a helpful, fancy, friendly, innocent, outstanding, courageous, thoughtful person who loves writing and wants to share my knowledge and understanding with you.